የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለላይት ሀውስ ጋርመንት ማኑፋክቸሪንግ ፒኤልሲ በአዳማ ኢንደስትሪያል ፓርክ የ5ሺ 500 ሜትር ካሬ የማምረቻ ሼድ አከራየ።
ከኮርፖሬሽኑ ጋር ውል የገባው ይህ ኩባንያ በዋናነት ወታደራዊ አልባሳትን የሚያመርት ሲሆን ሌሎች የተለያዩ አልባሳቶችንም ያመርታል።
ኩባንያው ከ216 ሚሊየን በላይ በሆነ በጀት ስራውን እንድሚጀምርም ተገልጿል።
በብሩክ ያሬድ
2022-09-22
