ሀገሬ ቲቪ

የሱዳን ታጣቂዎች የምግብ ዘረፋ

የሱዳን ታጣቂዎች በዳርፉር የሚገኘውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን ዘረፉ፡፡ በመጋዘኑ የተከማቸ 1 ሺሕ 900 ቶን የምግብ ውጤቶች በታጣቂዎቹ መዘረፉ ተነግሯል፡፡ በግጭት እና በጥቃት እየታመሰ በሚገኘው የሀገሪቱ ምዕራባዊው ክልል ነው ዘረፋው የተከሰተው፡፡ የሰሜን ዳርፉር ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው የኤል-ፋሸር ከተማ ዘረፋው በተካሄደበት ዕለት በመጋዘኑ አቅራቢያ ከባድ ተኩስ መፈጸሙን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የዓለም ምግብ ፕሮግራም ታጣቂዎች የተዘረፈውን ንብረት በማጣራት ላይ መሆናቸውን ዘኢስት አፍሪካ አስነነብቧል፡፡ እንደ ተባበሩት መንግሥታት ደርጅት ከ14 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የሱዳን ህዝብ ማለትም አንድ ሶስተኛው በሚቀጥለው አመት ሰብዓዊ እርዳታ የግድ ያስፈልገዋል፡፡ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2003 ጀምሮ በዳርፉር በተከሰተ የጎሳ ግጭት ከ 3መቶ ሺ በላይ ሰዎች ሲሞቱ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ የሚሆኑት ተሰደዋል፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-30