ሀገሬ ቲቪ

በዓለማችን 800 ሚሊየን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል

በዓለማችን 800 ሚሊየን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተገለጸ። ከተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን በተካሄድ ዓለም አቀፍ የምግብ ጉባኤ ላይ ነው ይህ የተገለጸው።

አፍሪካ ህብረት አውሮፓ ህብረትና አሜሪካ በትብብር ባዘጋጁት በዚህ ጉባኤ ላይ እንደተነገረው አፋጣኝ ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ ካልተሰራ ዓለማችን ብዙ ስዎችን በርሃብ ምክንያት ታጣለች።

በመሆኑም መንግስታት የረድኤት ድርጅቶች ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ድጋፍ ማሰባሰቡ ላይ ሊተጉ ይገባል ተብሏል።

በብሩክ ያሬድ
2022-09-22