ከሁለት ዓመት በፊት የዓለምን ቀልብ የገፈፈ አንድ ወረርሽኝ መከሰቱ ተሰማ። የኮሮና ቫይረስ። ይኸው ቫይረስ በጥቂት ጊዜአት በርካታ ሀገራት ላይ በመዛመት ከ 6ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል።
የዚሁ ቫይረስ መነሻ ደግሞ ቻይና እንደኾነች ይታመናል። ቫይረሱ ከታወቀ አንስቶ ሀገራት ሲያደርጉ የነበረውን ጥብቅ ቁጥጥራቸውን እየቀነሱ ቢመጡም ቻይና ግን እንዳጠነከርች ዘልቃለች ከዚሁ ጋር ተያይዞ በቻይና በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ወደ ማቆያ በማጓጓዝ ላይ የተከሰተው ኹነት ብዙዎችን አስገርሟል።
ነገሩ እንዲህ ነው በኮሮና ቫይረሳ የተያዙ የተወሰኑ ቻይናውያን ሲቹዋን ወደሚገኘው ለይቶ ማቆያ ሊወሰዱ ባስ ውስጥ እንዲገቡ ይደረጋል።
እነዚህ ዜጎች ታዲያ ለይበልጥ ትንቃቄ ታስቦ ቫይረሱን መከላከያ ልብስ ከእግር ጥፍራቸው እስከ ራስ ጸጉራቸው ተከናንበዋል። ኋላ ላይ ግን ባሱም ሳይንቀሳቀስ እንሱም ወደ ማቆእያው ሳይወሰዱ ውስጥ ላይ እንደተቆለፈባቸው ይቆያሉ።
በነገሩ ግራ የተጋቡት እነዚህ ቻይናውያን ባሱ ውስጥ ትርምስ፤ ግርግር፤ ጩኽት ይጀምራሉ፤ ግማሹ ክፈቱ ታፈንን ይላል በእድሜም ገፋ ያለው እረ መጸዳጃ ቤት መጠቀም እንፈልጋለን ከዚህ ባስ አስወርዱን ሲሊ፤ ልጅ የያዘውም ልጄ አለቀሰብኝ ክፈቱ እያለ ይለምናል።
የሚንከባከቧቸው የጤና ባለሙያዎች ግን ከዚህ ባስ መውረድ አትችሉም ወይ ፍንክች ያባቢላዋ ልጅ አሉ።በዚህ ድብልቅልቅ ባለ ባስ ውስጥ በቫየረሱ የተያዙት ቻይናውያን ለ 7 ሰዐታት እንዲሁ ሲወራጪ ባሱን ሲደበድቡ ቆዩ።
ይህን የባስ ውስጥ መተራመስ የሚያሳይ ተንቀሳቅስሽ ምስል የመንግሥት ኃላፊዎች ከተመለከቱ በኋላ ለተፈጠረው መጎሳቀል ይቅርታ አድርጉልን ብለዋል። እነዚህ የይድረሱልን ጥሪ ሲያሰሙ የነበሩ ቻይናውያንም ወደ ታሰበው የማቆያ ማዕከል ከሰዓት በኋላ እንዲገቡ ተደርጓል።
ይህ አጋጣሚ በተከሰተበት ተመሳሳይ ቀን ደግሞነገሩንም የሚያጣራ ቡድን እንደተቋቋመና እርማጃም እንደሚወሰድ ማሳወቃቸውን ከሳውዝ ቻይና ሞኒተሪንግ ፖስት የዜና ምንጭ ተመልክተናል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-09-22
