ሀገሬ ቲቪ

ሀያ ሜጋ ዋት የእንፋሎት ኃይል ማግኘት ተቻለ

ከአሉቶ ላንጋኖ ጥልቅ የከርሰ ምድር እንፋሎት ቁፋሮ ፕሮጀክት እስካሁን 20 ሜጋ ዋት የሚደርስ የእንፋሎት ኃይል መገኘቱን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

እስካሁን ቁፋሯቸው ከተጠናቀቀና የምርት ፍተሻ ከተደረገላቸው አምስት ጥልቅ ጉድጓዶች መካከል በአራቱ 20 ሜጋ ዋት የእንፋሎት ኃይል ተገኝቷል።

የጉድጓዶቹ ጥልቀት ከ 2700 እስከ 3000 ሜትር ይደርሳል ተብሏል። የ6ኛ እና የ7ኛ ጉድጓድ ቁፋሮ ስራም እየተከናወነም ይገኛል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-09-23