ሀገሬ ቲቪ

ሩሲያ በቁጥጥሯ ስር ባሉ የዩክሬን አራት ግዛቶች ህዝበ ውሳኔ ማካሄድ ጀመረች

በዚህ ህዝበ ውሳኔ ዶኔስክና ሉአንስክ ከምስራቅ ዩክሬን ኬርሶን አና ዛፓሮዚያ ከደቡብ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ለመቀላቀል አልያም በዩክሬን ስር ለመቆየት ደምጽ ይስጥባቸዋል ።

ለአምስት ቀናት የሚካሄደው ድምጽ የመስጠት ሂደት ከምዕራባውያን በዲሞክራሲ መቀለድ ነው በሚል ተቃውሞ ገጥሞታል።

ሩሲያ ግን ሁሉን ችላ ብላ ድምጽ ማሰጠት ጀምራለች ።ይህ የሩሲያ ውሳኔ የተወስኑ የዩክሬን ግዛቶችን እንደክሬሚያ ለመጠቅለል ያለመ ነው በሚል ተተችቷል።

በብሩክ ያሬድ
2022-09-23