ሁሌም የሰው ልጅ የፈጠራ ሰራ የሚጀምረው ችግሮችን ከመፍታት ነው ድሮኖች ወይንም ሰው አልባ አውሮፕላኖች በዚህ ችግርን ለመፍታት በተወጠነ እሳቤ የተፈጠሩ ናቸው ።
ድሮኖች የተፈጠሩ ሰሞን ለጥናትናለስለላ የሚሆን መረጃ ከማሰባሰብ የዘለለ ተግባር አልነበራቸውም ። በሚገጠሙላቸ ካሜራዎች እየተረዱ ከተፈለገው ቦታ መረጃን መቃረም ዋነኛ ስራቸው ነበር ። አሁን ግን ተግባራቸውም ሆነ ቴክኖሎጂያቸው አለ ልክ ሰፍቷል።
ከተራ የቀረጻ ተግባር አልፈው በጦር አውደማ ተገኝተው ኢላማቸውን ድባቅ የሚያገቡ ከሃገር ሃገር ተሻግረው የታዘዙትን ሁሉ የሚከውኑ ሆነዋል።
ቀላል ማህበራዊ አገልግሎት እንዲስጡ በማደረግ አማዞን ቀዳሚው ነበር ከደንብኞቹ የታዘዙ የኦንላይን ግዢዎችን በፍጥነት ያድርሱልኛል በሚል አሁን ደግሞየቻይናዋ ሸንዝን ድሮንን ለምግብ አቅርቦት በመጠቀም ሰሟ ገኗል።
በቀን 80 ሺ የምግብ ትእዛዝ በድሮን በማደረስ ።በከተማዋ በደሮን የምግብ ማደረሱን ተግባር የሚከውነው ተቋም ኃላፊ ያንግ ጁንዊ በሁሉም ነገር ድሮኖቹ ተመራጭ እንደሆኑ ነው የሚናገረው።
ለቀድሞዎቹ አድራሽ ሰራተኞች በ3 ኪሎሜትር ርቀት ምግብ ለማድረስ የፈለገ ቢፍጠኑ 30 ደቂቃ ይፈጅ የነበረው አሁን በድሮኖቹ በግማሽ ተቀንሶ በ15 ደቂቃ ነው የሚደርሰው ያውም ከሙሉ ዋስትና። ይህ ተግባር በከተማዋ ተወዳጅ መሆኑ የሽንዘን ሰማይ በድሮን እንዲሞላ አድርጎታል ።
ይሁን እንጂ አገልግሎታቸው መልካም ነውና እንደጦር ድሮኖች ቀልብ አይገፉም። ከዚያ ይልቅ የኔን ስንቅ የያዘው የቱ ነው በሚል ነዋሪዎች በጉጉት የጠብቁታል እንጂ ።
ይህን በሽንዘን ውጤታማ የሆነ የዴሊቨሪ አገልግሎትን በድሮን የማቀላጠፍ ተግባር የሌሎች አጎራባች ከተሞችንም ቀልብ ስቧል በቶሎ ወደኛም መስፋፋት አለበት የሚሉ መብዛታቸውን ሳውዝ ቻይና ሞርኒግ ፖስት አስነብቧል።
በብሩክ ያሬድ
2022-09-23
