ሀገሬ ቲቪ

አረንጓዴ አሻራ የቀጠናው አገራት የትብብር መስክ እንዲሆን ኢትዮጵያ እየሰራች ነው

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አረንጓዴ አሻራ የቀጠናው አገራት አንድ የትብብር መስክ እንዲሆን ኢትዮጵያ እየሰራች መሆኑን ገለጹ።

ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ እያከናወነች ያለውን የአረንጓዴ አሻራ ስራ እና የተገኙ መልካም ተሞክሮዎቿን ያካፈለችበት ውይይት በኒውዮርክ ተካሂዷል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ንግግር የአለም አየር ንብረት ለውጥ በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ልማት እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንዲሁም ድህነትን ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት ላይ ከፍተኛ ተግዳሮት መደቀኑን ገልፀዋል።

ውይይቱን የኢትዮጵያ መንግስት ከመንግስታቱ ድርጅት የልማት ኘሮግራም ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ነው።

በአብርሃም በለጠ
2022-09-23