
የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማሕበረሰብ ኤኩዋስ በጊኒ ላይ ማዕቀብ ለመጣል ተስማማ። ምዕራብ አፍሪካ ሀገራት መሪዎች በጊኒ ያለው ወታደራዊ መንግስት ወደ ሲቪል አስተዳደር እመለሳለሁ ያለበትን ጊዜ እየለዋወጠ በማስቸገሩ ነው ይህን ውሳኔ ያሳለፉት።
በመፈንቀለ መንግስት ሳቢያ ከታገዱት ማሊ ቡርኪናፋሶና ጊኒ በስተቀር ለዚሁ ሲባል ከተባበሩት መንግስታት ስብሰባ ጎን ለጎን በተካሄደው ስብሰባ የቀጠናው ሀገራት መሪዎች ተሳትፈዋል።
ኩዋስ ከመፈንቅለ መንግስቱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለቸውንም ለይቶ ተጨማሪ ማዕቀብ እንደሚጥል አስታውቋል።
በብሩክ ያሬድ
2022-09-23