ኢትዮቴሌኮም መስከረም 16/2015 ዓ.ም ሊድ/መሪ ሲል ስያሜ የተሰጠውን የ3 ዓመት የዕድገት ስትራቴጂውን ዛሬ አስታውቋል። በነዚህ ሶስት ዐመታት ተቋሙ ልሰራ ያሰብኳቸው በርካታ ሥራዎች አቅጃለሁ ብሏል።
የደንበኞች ብዛትን በ10.3 በመቶ በመጨመር 73.5 ሚሊየን ማድረስ ፣ከገቢ አንፃርም በ2015 በጀት አመት አጠቃላይ የገቢ መጠንን በ22.4 በመቶ በማሳደግ 75.05 ቢሊየን ብር ለማድረስም እቅድ መያዙን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩ ተናግረዋል።
ይህ የተዘጋጀው የሶስት አመት መሪ የእድገት ስትራቴጂ የመቋቋሚያ ደንብን እንዲሁም የቴሌኮም ገበያው ለውድድር ክፍት መሆኑንም ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ ነው።
በተጨማሪ ለንግዱ ማህበረሰብ ለየት ያለ አገልግሎት ለመስጠትም ተቋሙ አቅዷል ፤ ከኮምኒኬሽን ሥራዎች ባለፈ የ “ስማርት ሲቲ” እና ግብርና ለመገንባት ዝግጅት ማጠናቀቁን ሰምተናል። እነዚህ ግባታዎች ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረጉ በመኾናቸው ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው ተብሏል።
ኢትዮቴሌኮም ከኢትዮጵያ ባለፈ ወደ ጎረቤት እና ሊሎች ሀገራት አገልግሎቱን የማቅረብ ዕቅድ በዚህ የሦስት ዐመት ስትራቴጂው መካተቱን ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩ አብራርተዋል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-09-26
