በመላው ሀገሪቱ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ መስከርም 16 የሚከበር ነው የመሰቀል ደመራ በአል።
የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ከርስቲያን በአደባባይ ከምታከብራቸው በአላት አንዱ የሆነው የመሰቀል ደመራ በአል በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተቸረውም ነው ።
በተለይ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የሚከበረው የደመራ በአል በተባባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ተቋም (UNESCO) በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበ ነው ። የዚህ በአል ድምቀት የሆኑት ደግሞ የሰንበት ትምሀርት ቤት ወጣቶች ናቸው ።
በበአሉ እለት የምሰጋና ልብሳቸውን ለብሰው የተለያዩ ቤተ ክርስቲያንን የሚገልጹ ትርኢቶችን ያቀርባሉ ።ይህን ትርኢት ለማቅረብ ግን ከወራቶች በፊት ከየአጥቢያው የተውጣጡ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች በአንድ ተሰባሰበው ይዘጋጃሉ።
እኛም በአለቱ በስሜን እና በምአራብ አዲስ አበባ የሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ዝግጅት ሲያደርጉ ተገኝተን ትርኢታቸው ምን መልክ እንዳልው ጠይቀናቸው ነበር ።
እነዚህ ወጣቶች ከ 1ሺ 600 በላይ ናቸው ። እንደዚሁ ሁሉ በሌሎችም ቦታዎችም ለደመራ በአል የሚዘጋጁ እንዳሉ ነው የተገለጸልን።
በእነዚህ ወጣት ሰንበት ትምሀርት ቤት ተማሪዎች ውብ ዝግጅት እንዲሁም በቤት ክርስቲያን አባቶች ድንቅ ያሬዳዊ ዝማሬ እና ጸሎት ፣ ደምቆ የሚከበረው በጉጉት የሚጠበቅ በአል ነው።
በወንድምአገኝ አበበ
2022-09-26
