ዓለማችን ትልቅ ችግር ውስጥ ነች። ፕላኔታችንም እየተቃጠለች ነው ፤ ረሃብ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ አስከፊ ደረጃ ላይ ደርሷል ፤ ጦርነት በሁሉም ቦታ እየተፋፋመ ነው ፤ ሰብዐዊ መብቶች ተረግጠዋል ፤ ሰዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ እየተጎዱ ነው ።
ሁኔታው በጣም ያሰጋል ያሳዝናልም። ይህ ባሳለፍነው ቅዳሜ በኒዎርክ በተኪያሄደው አሥረኛው እኛ ዓለም አቀፍ ዜጎች ነን ( ግሎባል ሲቲዝን ፌስቲቫል) ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ የተናገሩት ነው።
እኛ ዓለም አቀፍ ዜጎችን ነን ( ግሎባል ሲቲዝን ) በዐለማችን የሚከሰቱ ችግሮችን በመቅረፍ ሁሉም ዜጎች አንድ ሆነው ተመሳሳይና የተመቻቸ ኑሮን በየአካባቢያቸው እንዲኖሩ ማስቻልን አላማ አድርጎ ከዛሬ አስር ዐመት በፊት የተቋቋመ በ የዓመቱ የሚከበር ንቅናቄ ነው።
በዓሉ ከመንግሥት፣ ከድርጅቶችና ከበጎ አድራጎት ማህበራት ድህነትን ለማሸነፍ፣ እኩልነትን ለመጠየቅና ምድርን ክጥፋት ለመከላከል የሚያስችሉ የገንዘብ ድጋፎችን ለማግኘት የተባበሩት መንግሥታት ዐመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ባደረገ በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ ይከበራል ።
ባሳለፍነው ቅዳሜ 10ኛ ዐመቱን በኒዎርክ ባከበረው በዚህ በዐል ዐለማችን ላይ የተከሰቱ በርካታ ጉዳዮች ተነስተውበታል ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ ዓለማችን ያስተናገደቻቸውን እያንዳንዷን ችግሮች የፈጠርነው እኛው ነን የሚፈቱትም በኛው ነው ብለዋል ።
አንድ ነገር መናገር እችላለሁ እኛ ተስፋ የሌለን ሰዎች አይደለንም ። ህይወታችን በተስፋ የተሞላ ነው ። ፍጹም ሰላም የሰፈነባት ፤ የተራበ ህዝብ የማይታይባት ፤ የጦርነት ድምጽ የማንሰማባትን ዓለም መፍጠር ፈጽሞ የማይችል ነገር አይደለም ሲሉ በመድረኩ ላይ ተናግረዋል።
ከድህነትና ከረሃብ የጸዳ እውነተኛ ሰላም የሰፈነበት ዓለምን መፍጠር ተመድ የ 2030 ዕቅዱ አድርጎ እንቅስቃሴዎችን ጀመሯል ነገር ግን እየሆነ ያለው ነገር ጊዜ የሚሰጥ አይደለምና ከአሁኑ ሰዐት ጀመሮ ሁሉም በየፊናው መረባረብ አለበት ብለዋል ።
በመድረኩ የተሰበሰቡትን ዜጎችንም ድምጻችሁ ለውጥ ያመጣልና የፆታ እኩልነትን ፤ ፈጣን የአየር ንብረት እርምጃዎችን ፤ ሰላምን ና ማኅበራዊ ፍትሕን እንዲሰፍን ሁሌም መሪዎቻቸውን እንዲጠየቁ አሳስበዋል።
በመደርኩ ይህን ሃስብ የሚደግፉ በርካታ ወጣቶች ታደመዋል ።ታዊቅ የሙዚቃ ስዎችም ስራዎቻቸውን በመደርኩ አቅርበዋል።
በዮሴፍ ከበደ
2022-09-26
