ሀገሬ ቲቪ

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መልዕክት ለመስቀል በዓል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ደመራው ሲለኮስ ጨለማው በብርሃን፤ ቁርና ብርዱ በሙቀት፤ ድብርቱ በተስፋ ይተካል ብለዋል።

የመስቀል በዓል ያለፈውን ፈተና የምናስወግድበትና ለመጪው ተስፋ የምንሰንቅበት መሆኑን የአከባበሩ ሥነ ሥርዓትና የሽማግሌዎች ምርቃት ያሳየናል ያሉት ሚኒስትሩ።

ኢትዮጵያም በዚህ ዓመት የከረሙ ችግሮቿን እንድትፈታና ገበታዋን ለልጆቿ በሚያስፈልጋቸው ምግብ እንድትሞላ፣ ኢትዮጵያን የምንወድ ሁሉ ቆርጠን እንድንነሣ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ አቀርባለሁ ብለዋል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-09-26