በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የተከሰተውን ቀውስ ለመቋቋም በሀገራችን የተጀመረው የኤለክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ማምረት መልካም አጋጣሚ መሆኑ ተገለጸ።
ይህንን የገለጸው በሀገራችን የኤለክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በመጋጣጠሙ ዘርፍ እየተሳተፈ ያለው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ነው።
ሃገራችን የግድብ፣ የንፋስ እና የጂኦተርማል የታዳሽ ኃይል አቅሞቿን በመጠቀም የኤለክትሪክ ተሽከርካሪዎችን መጠቀም የሚያስችላትን ዕድል ልታባክን እንደማይገባ አትሌቱ ጠቁሟል።
የነዳጅ አቅራቢ እና የነዳጅ መኪኖች አምራች ሃገራት ዓለም ሌላ አማራጭ እንዳታይ ተጽዕኖ ማሳደራቸውን የገለጸው አትሌቱ የኤለክትሪክ መኪኖች ለነዳጅ የሚወጣን የውጭ ምንዛሬ እንደሚያስቀሩም የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው ወርክ ሾፕ ላይ ተናግሯል።
በአብርሃም በለጠ
2022-09-26
