
በዩጋንዳ ተላላፊ በሆነው በኢቦላ ቫይረስ በአጠቃላይ 16 ሰዎች ሲያዙ ሌሎች 18 ሰዎች ደግሞ በሽታው ሳይዙ እንዳልቀረ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ ።
እስከ አሁንም በቫይረሱ ምክንያት አራት ሰዎች የሞቱ ቶሎ እልባት ካልተገኝለት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል።
በአሁኑ ጊዜ ይህ ወረርሽኝ ወደ ሦስት አከባቢዎች የተዛመተ ሲሆን ሁሉም በማዕከላዊ ኡጋንዳ መሆናቸው ተጠቁሟል። የሀገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኤማ አይኔቢኦና እንደገለጹት ህዘባዊ ሰብሰባ እና የጉዞ እገዳ በማዕከላዊ ኡጋንዳ ተከልክሏል።
በብሩክ ያሬድ
2022-09-26