ሀገሬ ቲቪ

የኮሎኔል መንግሥቱ የኃዘን መግለጫ

ኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማርያም በአምባሳደር ዶክተር ካሣ ከበደ ህልፈት አዝኛለሁ አሉ፡፡ የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የአምባሳደሩ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ መፈጹሙን ተከትሎ ነው ። " የጓድ ዶክተር ካሣ ከበደን ሕልፈተ ሕይወት በመስማቴ ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል” ብለዋል፡፡ ጓድ ካሣ በሥራ ዘመናችን ሁሉ አንድም ቀን ያልተለየኝ የትግል አጋሬ ወንድሜ ነበረ ሲሉም ሀዘናቸውን ገልጸዋል፡፡ እሱን የመሰለ ድንቅ የፈጠራ ችሎታ ያለው ታታሪ ሠራተኛና ሀገሩን የሚወድ ወንድማችን ሲለየን ሀዘኑ ከባድ ነው ብለዋል::

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-31