የመንገድ ልማት ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ያለው ጠቀሜታ በግልጽ የሚታይ ነው ።
በአዲስ አበባ ከተማ በብዙ ተገንብተው የተጠናቀቁ የመንገድ ፕሮጀክቶች እንዳሉ ሁሉ አንዳንድ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ግን ለአመታት ሲጓተቱ ቆይተዋል ፡፡
ከእነዚህ የመንገድ ፕሮጀክቶች አንዱ የአራራት ኮተቤ ካራ የመንገድ ፕሮጀክት አንዱ ነው ፡፡ የአካባቢ ነዋሪዎች በመንገዱ መጓተት ምክንያት ኑሯቸውላይ ጫና እንደፈጠረባቸው ይናገራሉ፡፡
የአራራት ከተቤ ካራ የመንገድ ፕሮጀክት በሁለት አመታት ግዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ቢባልም ስድስት አመት ፍጅቶም አልተጠናቀቀም ፡፡
የመንገድ ፕሮጀኮቱ የ6ኪ.ሜ ርዝመትና የ30ሜትር የጎን ስፋት ያለው ነው ፡፡ ፕሮጀክቱ በዚህ ደረጃ ለምን ተጓተተ ስንል የአዲስ አበባ መንገዶችን ባለሰልጣንን ጠይቀናል።
ባልሰጣኑ በመልሳቸው ‘መንገዱ ለሁለት ተቋርጮች የተሰጠ ቢሆንም ከኮተቤ ካራ የሚገኝው የመንገድ ፕሮጀክን የያዘው የመንገድ ተቋራጭ ግን መንገዱን በወቅቱ ማጠናቀቅ በለመቻላቸው እና መንገዱ የሚሰራበት አከባቢ ያለው የመሬት አቀማመጥ ምቹ አለመሆኑን እንደምክያት አንስትዋል።
ፕሮጀክቱ ሰኔ 30 2014 ዓ.ም ላይ ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረ ቢሆንም አሁንም አልተጠናቀቀም ።
ለመሆኑ መቼ ይጠናቀቅ ይሆን? ስንል ለጠየቅናቸው ጥያቄ በተያዘው የበጀት አመት ፕሮጀክቱን እንደሚያጠናቅቁ ነው የገለጹት ።
በወንድምአገኝ አበበ
2022-09-28
