ሀገሬ ቲቪ

ኖርድ 1 እና 2 የሩሲያ ግዝ አስተላላፊ መስመሮች ጉዳት ደረሰባቸው

ከሩሲያ ወደ ጀርመን በባልቲክ ባሕር ሥር የተዘረጉት ኖርድ 1 እና 2 የተሰኙት የሩሲያ ግዝ አስተላላፊ መስመሮች ጉዳት ደርሶባቸዋል ተባለ። የዴንማርክ የጦር ኃይል ይህንን የሚያረጋግጥ ተንቀሳቃሽ ምስል ይፋ አድርጉል። በዚህ ምስል በመስመሮቹ የሚጓዘው ጋዝ በባልቲክ ባሕር ላይ ሲንፎለፎል ያሳያል።

ሰኞ ዕለት ማታ የኖርድ2 ጋዝ ማስተላለፊያ መስመር ኦፕሬተር መስመሩ በድንገት ማፍሰስ መጀመሩን ሪፖርት ማድረጉ ተነግሯል።

ባለፈው ወር ወደ አውሮፓ ጋዝ ማድረስ ባቆመው በኖርድ 1 ላይ ሁለት ቀዳዳዎች ተገኝተዋል። ቦርንሆልም ደግሞክስተቱ የታየበት አካባቢ ነው።

ሩሲያእና ዩክሬን ጦርነት ውስጥ ከገቡ በኋላ ሩሲያ እነዚህን መስመሮች ጥገና ላደርግላቸው ነው በሚል ምክንያት በተደጋጋሚ ዘግታቸው ቆይታለች።

በዚህ የተነሳ የአውሮፓ ሀገራት በጋዝ እጥረት ሲታመሱ ቆይተዋል፤ እየታመሱም ይገኛሉ። ያለን ምርጫ ሩሲያን መለማመጥ ሳይኾን አማራጭ መፍትሔዎችን መፈለግ ነው በማለት ጋዝ ከሌላ ሀገር ማግኘት የሚችሉበትን መንገድ እየፈለጉ ይገኛሉ።

ኖርድ 1 እና2 የጋዝ ማስተላለፊያ መስመሮች ማፍሰስ መጀመራቸው ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረውን እና በትላንትናው ዕለት የተመረቀውን ከኖርዌ ወደ ፖላንድ የተገነባውን የባልቲክ ጋዝ ማስተላለፊያ መስመር ላይ መጥፎ ጥላ ያጠላ ነው ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

ይህ የጋዝ ማስተላለፊያ መሥመር አውሮፓን ከሩሲያ የጋዝ ጥገኝነት ያወጣል የሚል ተስፋ የተጣለበት ነው። የሚፈሰው የጋዝ መጠን በርከት ያለ እንደኾነ የዴንማርክ የኃይል ኤጀንሲ ኃላፊ ክርስቶፎር ቦትዛው ተናግረዋል።

የኖርድ 1 ጋዝ ማስተላለፊያ መሸንቆር ሰኞ ማታ ነው የተከሰተው በርከት ያለ መጠን ያለው ጋዝ እየፈሰሰ ነው ምናልባትም በየአንድሰዐቱ ሚሊዮን ኪውቢክ ሜትር ጋዝ ይፈሳል። በእርግጥ መስመሮቹ ጋዝ ማስተላለፍ አቁመዋል ነገር ግን ውስጣቸው ያልተሟጠጠ ጋዝ አለ እንደዚህ አይነት ጉዳት የመከሰቱ ሁኔታ በጣም የጠበበ ነው።

በጉዳዩ ላይ ሀሳቧን የሰጠችው ዩክሬን የጋዝ ማስተላለፊያ መሽመሮቹ መሸንቆር የሩሲያ የሽብር ጥቃት ውጤት ነው ስትል ተናግራለች። የተለያዩ የአውሮፓ ሀገር መሪዎች መስሮቹ ላይ የደረሰው ጉዳት ጉዳት ሆን ተብሎ ነው የሚል ሃሳብ ሰንዝረዋል።

የፖላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ማቴዎሽ ሞራቪየኪ ኾነ ተብሎ የተደረገ እና ከዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት ጋር የተያያዘ ነው ሲሉ መናገራቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

በተመሳሳይ የዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜት ፍሬድሪክሰን እከሌ ነው ያደረገው ብሎ መደምደም ቢከብድም በድንገት የኾነ አጋጣሚ አይደለም ብለዋል።

አሁን ላይ ታዲያ ሀገራት ጋዙ በሚፈስበት አካባቢ መርከቦች እንዳይጓዙ እያሳሰቡ ይገኛሉ።

በሙሉጌታ በላይ
2022-09-28