የ20ኛው ክፍለ ዘመን ድንቅ የህከምና ግኝት እንደሆነ ይነገራል፤ ፔኒሲሊን ። ፈጣሪው ደግሞ ከስትኮትላንዳዊ ደሃ ገበሬ ቤተሰቦች የተወለደው አሌክስ አንደር ፍሌሚንግ ።
አሌክሳንደር ለቤተስቦቹ 3ተኛ ልጅ ነበር ።የአሌክስ አንደር አባት ፈለሚንግ በአንድ አጋጣሚ በአከባቢው ለሚገኝ ባለሃብት በዋሉት ውለታ ምክንያት አሌክስአንደርን ባለሃብቱ ለማሳደግ ወሰደው ።
ለስዎች በአደራ የተስጠውም አሌክስአንደር ፍሌሚንግ የመጀመሪያ እና የሁለትኛ ደረጃ ትምሀርቱን ተምሮ እንደጨረሰ በወንደሙ ጉትጓችነት ለንደን የሚገኝወን ሴንት ሜሪ የህክምና ኮሌጅን ተቀላቀለ።
ሃገሩ በሪታንያ በመጅመሪያው የአለም ጦርነት ስትሳተፍ እርሱም በሮያል የጦር አካድሚ ወስጥም በሕክምና በባልሞያነት አገለገሏል። ከዚህ በተጨማሪም እሱና በርካታ የሥራ ባልደረቦቹ በፈረንሳይ ምዕራባዊ ግንባር በሚገኙ የጦር ሜዳ ሆስፒታሎች ውስጥ በሀክምና አገልገልውም ነበር ።
ከመጅመሪያው የአለም ጦርንት በሃላም በ1918 ወደ ሴንት ሜሪ ሆስፒታል ተመልሶ የነበርው አሌክሳንደር በ1928 ዓ.ም. የለንደን ዩኒቨርሲቲ የባክቴሪዮሎጂ ፕሮፌሰር ሆኖ ተመረጠ ።በዚ አጋጣሚ ነበር ታዲያ አሌክስአንደር ፍለሚንግ በህክምናው ዘርፍ እንደት ትልቅ እምርታ ሚታየውን የመጀመሪያው ጸረ ባክቴሪያ የሆነው ፔኒሲሊን በ1928 ዓ.ም. ያገኘው።
አሌክስ አንደር ፈሌሚንግ በአንድ ወቅት ከ እረፍት ወደ ስራው በተመለሠበት ወቅት ስታፋይሎኮከስ የተባለውን ባክቴሪያ ለማጥናት አዘጋጅቶ ሳይከድነው ያስቀመጠውን ሳህን ሲመለከት በውስጡ የነበረው ሻጋታ ብዙዎቹን ባክቴሪያዎች እንደገደላቸው ተመለከት ።
ሻጋታውን ሲመለከት ፔኒሲሊየም ኖታቱም እንደሆነ አገኘው ።በተከታታይ ጥናትም ሌሎች ባክቴሪዎችን መግደል እንደሚችል አረጋገጠ ።
አሌክስአንደር በሁለተኛው የአለም ጦርነት ምክንያት የጅመርውን ጥናት አቋረጠ። የመጅመሪያ ጥናት ካቋረጠ ከ 10 ዓመት በኋላ የአወስትራሊያ ሳይንቲስቶች ሐዋርድ ፍሎሬ እና ኸርነስት ቼይን ጥናቱን እርሱ ከቆመበት በመቀጠል ባክቴሪያ ገዳይ የሆነውን ፔኒሲሊንን ለይተው አገኙት ።
ከዚህም በኋላ ዓለምን የለወጠ ግኝት በመባል በ1948 ዓ.ም. በፊዚዮሎጂ የኖቤል ሽልማት ዘርፍ አሸናፊ በመሆን ሽልማቱን ለሶስት ተጋርተዋል ።
በአሁን ዘመንም በስፋት ለህክምና እያዋለ የሚገኘው ጸረ ተህዋስያን መድሃኒት ፔኒሲሊን የተገኘው በዛሬው ቀን በ1921ዓ.ም. ነበር ።
በወንድምአገኝ አበበ
2022-09-28
