ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ። ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሃሰን ሸክ መሐመድ እና ልዑካቸው ከሀገራችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና ልዑካቸው ጋር መክረዋል።
ሀገራቱ የሚያጋጥሟቸውን የጋራ ችግሮች ለመፍታት የሁለትዮሽ ትብብር እንደሚያስፈልጋቸው የተናገሩት ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼክ መሐመድ የተሻለች ሶማሊያን ለመፍጠር ኢትዮጵያውያን የከፈሉትን መስዋዕትነት አድንቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በበኩላቸው ጠንካራ እና የተረጋጋች ሶማሊያ ለኢትዮጵያ ጥንካሬ አስፈላጊ መሆኗን ጠቁመው ኢትዮጵያ ከአዲሱ የሶማሊያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።
በአብርሃም በለጠ
2022-09-28
