ሀገሬ ቲቪ

የድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ የቀብር ስነ ስርዓት ነገ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል

የድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ ሐሙስ በመንበረ ጸባኦት ቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተገለጸ።

በስነስርዐቱ በወዳጅነት አደባባይ የክብር ሽኝት እንደሚደረግለት የተነገረ ሲሆን የቀብር ስነ ስርዓቱም ከቀኑ በስምንት ሰዓት ይፈጸማል።

ድምጻዊው በትላንትናው ዕለት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወደሚገኝ የግል ክሊኒክ ከሄደ በኋላ ህይወቱ ማለፉ ይታወቃል። ህይወቱ ካለፈበት ክሊኒክ ወደ አቤት ሆስፒታል ተወስዶ የአስክሬን ምርመራ ማድረጉን የ አ.አ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ሀገሬ ቴ.ቪ.ም ለድምጻዊው ቤተሰቦች፣ ወዳጆች እና አድናቂዎች መጽናናትን ይመኛል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-09-28