ሀገሬ ቲቪ

ኮንጎ የቀጠናውን ጦር ለመቀበል

ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የቀጠናውን ጦር ለመቀበል ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች። ሀገሪቱ ጥቃት እያደረሱ ያሉ አማጺ ታጣቂዎች ላይ የተቀናጀ እርምጃ ለመውሰድ እንዲያስችላት ነው የቀጠናውን ጦር ለመቀበል ዝግጁ የሆነችው።

በኮንጎ ከ120 የሚልቁ ታጣቂ ቡድኖች አሉ። ሀገሪቱ የምትቀበለው ጦርም የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ አባል ሀገራት ጦርን ነው። በዝግጅቱ ኮንጎ ቀድመው የሚደርሱት የኬንያ መከላከያ ሰራዊት አባላት እንደሆኑ ተጠቁሟል።

የኬንያ ኃይሎች እንደምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ(EAC) ኃይልነታቸው ኮንጎ በኪቩ እና ኢቱሪ ግዛቶች የምታደርገውን የደህንነት ትግል ያግዛሉ ተብሏል። የቡሩንዲ ኃይሎችም ቀደም ብለው የሀገሪቱን ጸጥታ ለማገዝ ገብተዋል። መረጃው የዘ ኢስት አፍሪካን ነው።

በአብርሃም በለጠ
2022-09-28