ሀገሬ ቲቪ

የዩክሬይን ህዝበ ውሳኔ

በዩክሬን አራት ግዛቶች በተካሄደ ህዝበ ውሳኔ ሁሉም ከሩሲያ ጋር መሆንን መምረጣቸው ተገለጸ።

በዶኔስክ 99 በሉሃንስክ 98 በዛፖሪዚያ 93 በኬርሶን 87 በመቶ የሚሆኑ መራጮች ከዩክሬን ይልቅ ሩሲያን መምረጣቸው ይፋ ተደርጓል።

ሆኖም ህዝበ ውሳኔው ድምጽ ለመስጠት መውጣት ከነበረበት ህዝብ 50 በመቶው ብቻ የተሳተፈበት ነው ተብሏል ። ወትሮውኑ በህዝበ ውሳኔው ተቃውሞ ሲያሰሙ የነበሩ ምዕራባውያን ውጤቱም አሳማኝ አይደለም በሚል ተችተውታል።

በብሩክ ያሬድ
2022-09-28