ሀገሬ ቲቪ

ዝናብ የቀላቀለ አውሎነፋስ አሜሪካን መታ

ሀሪኬይን የተሰኘው አውሎ ነፋስ የአሜሪካዋ ፍሎሪዳ ከተማን አጠቃ። በፍሎሪዳ ደቡብ ምዕራብ የባህር ዳርቻ ላይ የተከሰተው ዝናብን የቀላቀለው አውሎነፋሱ በሰዓት 250 ኪሜ እየተጓዘ በርካታ ቤት እና ንብረቶችን አውድሟል።

ይህ በታሪክ አሜሪካን የመታ ከባዱ አውሎ ነፋስ ስለመሆኑም እየተነገረ ነው። በፍሎሪዳ የሚገኙ ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው ስለመውታታቸውም ተሰምቷል። በከተማዋ ያሉ የኤሌክትሪክ መስመሮች አገልግሎት አቁመዋል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-09-29