የኮቪድ 19 ቫይረስ አለምን እና መላዋን ያሳዘን ክፉ በሽታ ነው ። ብዙዎች አዝነዋል በዙዎች ተከፍተዋል ። በማዘናቸው በቻ ሳይበቃ የሚወዷቸውን ሰዎች በስራአተ ቀብር መሰናበት እንኳን ያልቻሉበትም ግዜ ነበር ።
ዛሬ ታዲያ አንድ አሰገራሚ ሁነት እንነግራችኋዋለን ። ነገሩ የተፈጠረው በህንድ የኢንድስትሪ ከትማ በሆነችው አተር ፕራዴሽ በምትባል ከትማ ወስጥ ነው ።
ቪምሌሽ ሶንካር የተባለ አንድ ወጣት ሚያዝያ 19 ቀን 2021 ወደ ታሞ ወደ ሆስፒታል ይገባል። የህከምና በለሞያወችም ለቪምሌሽ ሶንካር በኮቪድ እንደትያዘ ለቤተሰቦችሁ ያሳውቃሉ ።
ታዲያ ቫምሌሽ በሶሰትኛው ቀን በኮቪድ 19 ሳቢያ ከዚህ አለም ይሰናበታል ። የሆስፒታሉ የማህደር ክፍልም ልጃቸው መሞቱን ለቤተሰቡ አሳወቆ የሞት ምዝገባ ሰርተፈኬት ሰጥቶ ይሽኛችዋል ።
ነገሩ ታዲያ እዚ ጋር ነው ሚስያስገርመው የሟች ቫምሌሽ ቤተሰቦች ልጃችን በህይወት አለ ኮማ ወስጥ ነው ይነቃል እናስታምመዋልን ብለው ወደ ሌላ ሆስፒታል ይወስዱታል ። በተመሳሳይ ሁኔታ ሌላኛውም ሆስፒታል ልጃቸው መሞቱን ያረጋግጥላቸዋል።
የሞች ቤተሰቦች ግን ኦክሲ ሜትር በተባለ ኦክሲጂን መለኪያ የቫምሊሽ የደም ዘውውሩ አለተቋረጠም በማለት ልጃችን ይነቃል እንቅልፍ ላይ ነው በማለት ወደ ቤታችው ወሰደታል ።
ሟች በሚሰራበት መስሪያቤት እንደታመመ እና ከህመሙ ሲያገገም ወደ ሰራ ገበታው እንደሚመስልሰ እየተጠበቀ እንደ ነበር አንድ የአከባቢው የፖሊስ መኮንን ለኢኒዲያን ኢክስፕረስ ገልጸዋል ።
የሟች ቤተሰቦችም የልጃቸውን አስክሬን እየተንከባከቡ ለ አንድ አመት ያህል በቤታቸው አኑረወታል ። ቤተሰቡም በህይወት ያለ ለሚመስላቸው የልጃቸው አሰክሬን በ የ ቀኑ 3 ግዜ በጸረ ጀርም እንዲሁም በቀን 3 ጊዜ ልብሱን እይቀየሩ እንድሁም የ24 ሰአት የኦክሲጂን ሲልንደር በምግጠምም ይጠበቁት ነበር ።
ለርጅም ጊዜ በህክምና ላይ እንድሆን የሰማው የሟች መስሪያቤት ቫምሊሽ ያለበትን ሁኔታ ለማጣራት የላከው ቡድን ግን ቤት ወስጥ ሲደርስ የትመለከትው ነገር ግን ያልጠበቁት ነበር የሟች አሰከሬን ሰውነት ሰጋው እይተራገፈ እና አጥንቶቹ በመታየት ላይ ነበር ።
ይሀን የሰማው የአከባቢው ፖሊስ ደርሶ አስክሬኑ በመውስድ በእምንታችው መሰርት አቃጥሎታል ። ፖሊሶቹም እንዳሉ እዚህ ላይ ምንም የተሰራ ወንጀል የለም ግን ቤተሰቦችሁ ልጃቸው መሞቱ እና አስክሬኑ መቃጥሉን ሊያምኑ ይገባል በሎአል።
በወንድምአገኝ አበበ
2022-09-29
