ሀገሬ ቲቪ

የአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ሰርዐተ ቀብር ተፈጸመ

መስከረም 17/2015 ዓ.ም በድንገተኛ ሕመም ሕይወቱ ያለፈው የአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ በዛሬው ዕለት ሥርዓተ ቀብሩበመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤ/ክ ተፈጽሟል።

አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ አራት ተወዳጅ የሆኑ የመዚቃ አልበሞችን ለህዝብ ጆሮ ማደርስ የቻለ ሲሆን ። አርቲሰቱ ባለትዳር እና የአንድት ሴት ልጅ አባትም ነው ።

በማኅበራዊ ሕይወቱም ለበርካቶች መጠጊያ፣ ደግ፣ ሩህሩህ እና አዛኝ እንደነበር የቅርብ ወዳጆቹ እና የሙያ ባልደረቦቹ ይናገራሉ።

በቀበር ሰነ ሰርአቱ ላይ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ ሙያ አጋሮቹ፣ አድናቂዎቹ እና ወዳጅ ዘመዶቹ ተገኝትዋል ።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-09-29