ሳፋሪኮም ኢትዮጲያ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በአወዳይ እና በጎንደር ከተማ ማስጀመሩን አሰታወቀ ። ይህም የደንበኞች የኔትዎርክ እየተሞከረባቸው ያሉት ከተሞች ቁጥርን ወደ አስር እንደሚያደርሰው ነው የተገለጽው።
የጎንደር እና የአወዳይ ከተማ ደንበኞችም ከ07 የሚጀመረውን የሳፋሪ ኮም ኢትዮጲያ ሲም ካርድ በመግዛትም መጠቀም ይችላሉ ተበሏል።
የሳፋሪኮም ኢትዮጲያ ሲም ካርድ ደንበኞች ኔትወርኩን ለአንድ ወር ያህል እንዲሞክሩት የሚረዳ የደንበኝነት ማስጅመሪያ የዳታ፣የድምጸ እና የጹሁፍ መልዕክቶችን የያዘ ነው ።
ተቋሙ እንዳስትወቀው ከሆነ እስክ ሚያዚያ 2015 ድረስ ወደ 25 ከተሞች ላይ አገልግሎቱን እንደሚያስጅመር ነው ያሰታወቀው።
በወንድምአገኝ አበበ
2022-09-29
