ሀገሬ ቲቪ

ኢትዮጵያዊው ባለሀብት አፍሪካ ኢኮኖሚክ ቢውለደር ሸለማቸው

ለኢትዮጵያዊው ባለሀብት አቶ አይሸሽም ተካ አፍሪካ ኢኮኖሚክ ቢውለደር የተሰኘ የሽልማት ድርጅት እውቅና እና ሽልማት አበረከተላቸው።

ባለሀብቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ በደቡብ ሱዳን እና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በምጣኔ ሀብት ዕድገት ላይ እያበረክቱ በሚገኘው ተሳትፎ ነው እውቅና እና የክብር ሽልማት የተደረገላቸው።

አቶ አይሸሽም ከሽልማቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት ከቀን ሰራተኝነት ተነስቶ በአፍረካ ምጣኔ ሀብት ዕድገት አስመዝግቦ መሸለም መቻል ለአፍሪካዊያን ወጣቶች ተምስሌት ነው ብለዋል።

ድርጅቱ የአፍሪካን ኢኮኖሚ በመገንባት ትልቅ ድርሻ ላበረከቱ ታዋቂ አልሚዎች እውቅና ሲሰጥ ይህ ለ12ኛ ጊዜ ነው።

በዮሴፍ ከበደ
2022-09-30