ሀገሬ ቲቪ

የኢትዮጵያ ጽላቶች እንዲመለሱ የጠየቁት ሊቀ ጳጳስ

በእንግሊዝ የቀድሞው የካንተርቤሪ ሊቀ ጳጳስ ሎርድ ካሬይ በዌስት ሚኒስተር ገዳም የሚገኙ የኢትዮጵያ ጽላቶች እንዲመለሱ ጠየቁ። ሊቀ ጳጳሱ ታቦታቱን የእምነት ጉዳይ ሲሉ ከሰየሙ በኋላ ነው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የጠየቁት።

ታቦታቱ በ1860 ዓ.ም. አጼ ቴዎድሮስ ከእንግሊዝ ካደረጉት የመቅደላ ጦርነት በኋላ የተወሰዱ እንደሆኑ ይታመናል። የ86 ዓመቱ ሊቀጳጳስ ከወራት በፊት የእንግሊዝ ሙዚየም የወሰዱትን 11 ታቦታት እንዲመልሱ አሳስበው ነበር።

የኢትዮጵያ መንግስት ታቦታቱ እንዲመለሱ ጥያቄ ቢያቀርብም ውሳኔው ገዳሙ በንጉሱ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ስር ያለ በመሆኑ የንጉስ ቻርለስን ይሁንታ ይፈልጋል ሲል የዘገበው ደይሊ ሜይል ነው።

በአብርሃም በለጠ
2022-09-30