ሀገሬ ቲቪ

የናይጀሪያ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች ስምምነት

ሶስት የናይጀሪያ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዕጩዎች ሰላማዊ ቅስቀሳ ለማድረግ ተስማሙ። ስምምነታቸው በሀገሪቱ የሚደረገውን የ2023 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ቅስቀሳ ግጭቶችን ለማስወገድ ያለመ ነው ተብሏል።

በአፍሪካ ብዙ ህዝብ ባለባት ናይጀሪያ የተካሄዱ ቀደም ያሉ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫዎች በግጭት፣ በማጭበርበር፣ በፍርድ ቤት ተቃውሞ እና በዘውግ ውጥረት የታጀቡ ነበሩ። ቀዳሚ አራት እጩዎች ፕሬዝዳንት ሙሃመዱ ቡሃሪን ለመተካት ይፎካከራሉ።

የኢኮኖሚ ጫናዎች እና የጸጥታ ሁኔታ ለተተኪው ፈተና ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል። የዕጩዎቹን ስምምነት የሀገሪቱ ብሄራዊ የሰላም ኮሚቴ ያስተባበረው እንደሆነም ተጠቁሟል።

በአብርሃም በለጠ
2022-09-30