የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በሩስያ ላይ ለስምንተኛ ዙር ማዕቀብ ለመጣል የመነሻ ስምምነት አደረጉ። የአውሮፓ ህብረት ዋና ኃላፊ በሳምንቱ መጀመሪያ በሩስያ ላይ የንግድ ማዕቀብ እና ግለሰቦች ላይ ዕገዳ መጣል እንደሚገባ ምክራቸውን አስቀምጠው ነበር።
የአውሮፓ ህብረት ባሳለፍነው ሳምንት ሩስያ ኃይሏን በሰፊው በማንቀሳቀሷ ለተግባራዊ ምላሽ ቢነሳሳም ስምምነቱን ወደ ተግባር ለማስገባት ግን ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል እየተጠቆመ ነበር።
የኒውክሌር ስጋት፣ ሩስያ የዩክሬይን ግዛት የነበሩ ክልሎችን እጠቀልላለሁ ማለት ለህብረቱ ስጋት ሆነዋል ሲል የዘገበው ሮይተርስ ነው።
በአብርሃም በለጠ
2022-09-30
