ሀገሬ ቲቪ

የሩሲያ አዲስ ግዛቶች

መቋጫ አልባ የሚመስለው የዩክሬንና ሩሲያ ጦረነት ከሰባት ወራት በኋላ ጥቂት ለውጥ የሚባሉ ሁነቶችን እያስተናገደ ነው ለውጦቹ ከሰላም ይልቅ ጦረነቱን የሚያባብሱ ቢሆንም ይሀውም የዩክሬን ጦር ቀድሞ በሩሲያ እጅ ውድቀው የነበሩ ጥቂት ግዛቶችን ማስመልሱና ሩሲያ ደግሞ በአንጻሩ ባካሄድኩት ህዝበ ወሳኔ እኔን መርጠዋል ያለቻቸውን አራት የይኩሬን ግዛቶች በይፋ ልጠቀልል መሆኗን መግለጿ ።

ይህ የሩሲያ ተግባር ቀድሞም ከሃሳቧ በተቃራኒ የቆሙት ምዕራባውያን ይበልጥ እንዲያወግዟት ምክንያት ሆኗቸዋል ። እሩሲያ ጆሮ ባትሰጣቸውም።

የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን በግዛቲቱ ነዋሪዎች ምርጫ ማንም አየገባውም ብለዋል ለአምስት ቀናት በተካሄደ መርጫ በአራቱም ግዛቶች ማለትም በዶኔስክ፣ በሏንስክ፣ በዛፖሮዚያና ኬርሶንን ያሉ ነዋሪዎች 90 በመቶ በላይ እኛን መርጠዋል በሚል።

ለዚህም በይፋ ግዛት የመጠቅለል ስን ስርአት በክሬምሊን ለማካሄድ ሁሉ ነገር ተጠናቋል። ነገር ግን እስካሁን ባለ መረጃ በተለይ በዶኔስክና በዛፖርዚያ የሩሲያ ጦር ሙሉ በሙሉ ግዛቶቹንን በቁጥጥሩ ስር ማዋል አልቻለም። በዶኔስክ 60 በመቶውን ሲይዝ በዛፖሮዚያ ደግሞ 70 በመቶውን ነው የያዘው ።

በዛ ላይ ደግሞ የዩክሬን ጦር ከመቼውም ግዜ በላይ ተጠናክሮ ወደፊት እየተንደረደረ ነው ። ሩሲያ ሃይሏን ለማጠናከር በከፊል ተጠባባቂ ጦሯን እንደምትጠራ ብታስታውቅም በርካታ ዚጎቿ ጥሪውን እና ጦረነቱን ሽሽት ስደትን መርጠዋል እጁን ዘርግቶ የሚቀበላቸው የጎረቤት ሃገር ቢያጡም ጆርጃይን እንኳ ሳይቀር መርጠው እየሸሹ ነው ።

ፑቲን ግን ይህ ሁሉ ያስጭነቃቸው አይመስልም ግዛቶቹን የመጠቅለሉ ያፋዊ ሰነድ ክስአታት በኋላ በፊርማቸው እንደሚያጽድቁት ይፋ አድርገዋል።

የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ግን ጉዳዩ ህግን የጣሰ ነው በልዋል ተግባሩን አስመልክተው ለጋዜጠኖች በሰጡት ማብራርያ

“የተባበሩት መንግስታት ቻርተር ግልጽ ነው የአንድን ሉአላዊ ሃገር በሃይል ይዞ ለመጠቅለል የሚደረግ ሙከራ ህገውጥ ነው የደርጅቱን ቻርተር እና ዓለም አቀፍ ህግንም የጣሰ ነው። ሩሲያ ደግሞ በጸጥታው ምክርቤት ቋሚ መቀመጫ ካላቸው አምስት ሃገራት አንዷ ናት የድርጅቱን ቻርተር ማክበር ከሷ ይጠበቃል።”

ወትሮም ከዩክሬን ጎን የቆመችው አሜሪካ ይሄ ቀልድ ነው ሀገሬ በፍጹም አትቀበለውም ብላለች በፕሬዘዳንቷ በኩል

“ዩናይትድ ስቴት በፍጹም በፍጹም ሩሲያ የዩክሬን ሉዐላዊነትን ጥሳ ግዛቶቼ ናቸው ለምትላቸው ቦታዎች እውቅና አትሰጥም። የይስሙላ ህዝበውሳኔውም አሳፋሪ እጅግ አሳፍሪ ነው ውጤቱም በሞስኮ የተፈበረክ እንጂ የዩክሬን ህዝብ እውነታ አይደለም እንዲያማ ቢሆን በየቀኑ ለሃገራቸው ሉአላዊነት ምን አዋደቃቸው።”

ማንም ምን ቢል ከሰብኩት የሚገታኝ የለም ያለችው ሩሲያ ግን ከሰባት ዓመት በፊት እንደጠቀለለቻት ክሬሚያ እነዚህን ግዛቶችም መጠቅለላቸው አይቀርም ብላለች።

በብሩክ ያሬድ
2022-09-30