ሀገሬ ቲቪ

የቡርኪናፋሶ መፈንቅለ መንግስት

ሁሌም በመንግስት ለውጥ ሳቢያ ነውጥ የማያጣት ሀገር ብትሆንም ቡርኪናፋሶ ያሁኑ ግን በዛ ይላሉ ትንታኞች በአንድ ዓመት ውስጥ ለሁለትኛ ጊዜ መፈንቅለ መንግስት ሰላጋጠማት ።

ነጻነቷን እንደአውሮፓውያኑ የዘመን ቀመር 1960 ካገኘች ብኋላ ለ8ኛ ጊዜ የተካሄደመፍንቅለ መንግስት ነው ይህ ያሁኑ። የኩርው አፍሪካዊ የቶማስ ሳናካራ ሀገር ቡርኪናፋሶ ድንቅ መሪዋን በምዕራባውያና እና በውስጥ ባንዳዎች ትብብር ካጣች በኋላ አጥቂ አረጋግተው መምራት የቻሉት ብሌስ ኮምፓዎረ ብቻ ናቸው።

ከወራት በፊት በምርጫ ያሸነፉትን ፕሬዘዳንት ሮች ካቦሬን አባረው ስልጣኑን የተቆናጠጡት ሌተናል ኮለኔል ፖል ሀንሪ ዲምባ በሰፈሩት ቁና ሆኖባቸው በወጣቱ ካፒቴን ኢብራሄም ትራዎሬ እሳቸውም ከመንበራቸው ተፍንቅለዋል ።

ለነፍሳቸው በመሳሳትም በቀድሞ ቅኝገዥዋ ፈርንሳይ የጦር ካምፕ ውስጥ መደበቅን መርጠዋል። ይሁን እንጂ ለደህንነቴ ዋስትና ይስጥኝ እንጂ ስልጣኑን አልፈልግም ማለታቸውን እየተዘገብ ነው። ጉዳዩ ከሳቸው አፍ አይሰማ እንጂ የሀገር ሽማግሊዎችና የዕምነት ተቋማት ኮለኔሉ ይህን ማለታቸውን ተናግረዋል።

ቡርኪናውያን በኮለኔሉ መውረድ የከፋቸው አይመስልም ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ የፈየዱት የለም ሀገሪቱ የአማጽያን የታጠቁ ሃይሎች መፈንጫ ሆናለች ሲሉም ይወቅሷቸዋል። ለዚህም ይመስላል ተጠልለውባቸዋል በተባሉት ቦታዎችም ጥቃት ለመስንዘር የተንቀሳቀሱ ዜጎች የበዙት ።

አብዛኞቹ ዜጎች ግን ይህ በሃይል ስልጣን የመነጣጠቅ መንገድ አይጠቅምንም ባይናቸው ።ሁሉም ነገር በሀገሪቱ ህገምንግስት መሰረት ሊመራ የግባል በሚል ። መፍንቅል መንግስት ችግራችንን ያባብሰው ይሆናል እንጂ የሚፈይድልን የልም በሚል።

ለነገሩ ይህ የመፍንቅል ምንግስት መደጋገም ከሁሉም አካላት ውግዘት ነው የመጣበት ።የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳፋኪ መህማት ህብረቱ መፍንቅለ መንግስቱን እንድሚቃወም አስታውቀዋል የተባበሩት መንግስታት ዋና ጽሃፊ አንቶኒዮ ጉትሬዝም በተመሳሳይ ድርጊቱን አውግዘዋል።

የሀገሪቱ የቅድሞ ቅኝ ገዥ ፈረንሳይም ከአውጋዥዎች ጎን ቆማለች እርሷ እንኳን በኤንባሲዋ ላይ የደረስው ጥቃት አሳስቧትም ይሆናል።

በቀጠናው የመጀመሪያ ወጣት መሪ የተስኙትና መፍንቅለ መንግስቱን የመሩት ካፒተን ኢብራሄም ትራዎሬ አወግዦቻችወን የሰሙ አይመስልም የሃገራቸውን ህዝቦች ግን ተረጋጉ ሁሉ ነገር ጥሩ ይሆናል የተፍጠረ አዲስ ነገር የለም ወድ ቀድሞ ተግባራችሁም ተመለሱ እያሉ ነው። በዋና ከተማዋ ዋጋ ዱጉ በፈረንሳይ ተቋማት እየተወሰድ ያለ የሃይል እርምጃም እንዲቆም አዘዋል።

በብሩክ ያሬድ
2022-10-03