ሀገሬ ቲቪ

በ150 ሚሊዮን ብር የማህበራዊ አገልግሎት ተቋማት መልሰው ተገነቡ

በአማራ ክልል በሰባት ከተሞች ከህወሃት ጋር በነበረው ጦርነት ወድመው የነበሩ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት እንደገና መገንባታቸው ተገለጸ።

በኮምቦልቻ፣ ደሴ፣ ሸዋሮቢት፣ ከሚሴ፣ ወልዲያ፣ ሰቆጣ እና ላሊበላ መልሰው የተገነቡት ተቋማት የ150 ሚሊዮን ብር ወጭ ተደርጎባቸዋል ተብሏል።

በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ከተገነቡት ተቋማት ስምንት ትምህርት ቤቶች፣ ሶስት ጤና ኬላዎች እና 7 የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ተቋማት ይገኙበታል ሲሉ የመልሶ ግንባታው አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ ሙሴ ገልጸዋል።

ተቋማቱን ለመመረቅም የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በአብርሃም በለጠ
2022-10-03