የአሜሪካ ኢምባሲ ስልሳ በኦንላይን ጋዜጠኝነት ዘርፍ የሚሰሩ አካላት የሚሳተፉበት ዝግጅት አስጀመረ።
ቴክ ካምፕ አዲስ የተሰኘውን ይሄው ዝግጅት ለእውነታ አጣሪዎች ለጋዜጠኞች ለሶፍትዌር አበልጻጊዎች በሀገር ውስጥና በውጭ አስልጣኞች ስልጠና የሚሰጥበት ነው።
በዋናነት በምርመራ ጋዜጠኝነት በሞባይል ቪዲዮ ቀረጻና ቅንብር በእውነታ ማጣራት ዘዴዎች ላይ የተኮረ ስልጠና እንደሚስጥ ተገልጿል።
በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኢምባሲ አማካሪ ሩት አኔ ስቴቨን ክሊዝ በአሜሪካ መንግስት ድጋፍ የሚካሄደውን ዝግጅቱን በይፋ አስጀምረውታል።
ዝግጅቱ ጋዜጠኞች እና የዲጂታል ሚዲያ ተከታታዮች አሳሳችና የተዛቡ መረጃዎችን የመለየት አቅማቸው እንዲዳብር እንደሚያግዝ ተነግሯል።
በብሩክ ያሬድ
2022-10-03
