መንግሥት በሲሚንቶ ምርት ላይ የሚታየውን ‘’የተጋነነ’’ ሲል የጠራውን ዋጋ ለማረጋጋትና የሚመረተው ውስን ሲሚንቶ ፍትሀዊ በሆነ ሥርጭት ለኀብረተሰቡ ለማቅረብ የሲሚንቶ ግብይት መመሪያ908/2014ን አውጥቷል።
በዚህ መመሪያ በከተማዋ ሲሚንቶን ከፋብሪካው ቀጥታ ወደተጠቃሚው የሚያቀርቡት የኢትዮጵያን ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (ኢግልድ) ብቻ ኾነዋል።
እኛም ይህ የግብይት ስርዐት ምንይመስላል የሚለውን ለመቃኘት ወደ ሁለት ክ/ከተማዎች አቅንተን ነበር። በሕጋዊ መንገድ ከፋብሪካ ሲሚንቶ የሚጭኑ ተሽከርካሪዎች እንዲያደርሱ ከተመደቡበት ቀጠና ውጪ እያራገፉ መኾኑን የኮ/ቀ/ክ/ከ የንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብተየስ ዲሮታ ነግረውናል ሁሉንም መኪና መቆጣጠር አስቸጋሪ አድርጎብናል ብለውናል።
በተመሳሳይ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ የንግድ ጽ/ቤት እቴማር ጌታቸው የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ይህንን መመሪያ በመጣስ ሲሚንቶን በሕገወጥ መንገድ እየሸጡ መኾናቸው ቁጥጥር እንዳደረገው ተናግረዋል።
መንግሥት በሲሚንቶ ንግድ ውስጥ ያሉ አካፋፋዮች ከግብይቱ እንዲወጡ ቢያደርግም አሁንም ግን ሲሚንቶ የሚሸጡ ግለሰቦች አሉ ተብሏል በተጨማሪ ኀበረተሰቡ ሲሚንቶ ለማግኘት የግድ ሲሚንቶ እንዲሸጡ የተፈቀደላቸው ሁለት ድርጅቶች ወደ ሚገኙበት ሱቅ መሔድ ይኖርበትል ይህም ሌላው ተግዳሮት የኾነ ጉዳይ ነው።
አሁን ላይ በከተማዋ ሲሚንቶ የሚሸጡ የግል አከፋፋዮች ባለመኖራቸው የንግድ ሥራዎች እና ኢግልድ ባሏቸው ስምንት መሸጫዎች ነው እየተሸጠ የሚገኘው።
ሲሚንቶን ከሚፈልገው ተጠቃሚ ብዛት እና ከሱቆቹ ጥቂት መኾን የሚፈጥረውን ውጣውረድ እና እንግልት ለማስቀረት ምንታስባል ስንል በንግድ ሚኒስቴር የሀገር ውስጥ ንግድ እና ሸማች ጥበቃ መሪሥራ አስፈጻሚ የኾኑት መስከረም ባሕሩን ጠይቀናል።
እንዚህን ማከፋፈያ ሱቆች ማስፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት እንደሚደረግ እና ከፍተኛ የሲሚንቶ ምርት ተጠቃሚ ተቋማት እና ግለሰቦች ቀጥታ ከፍብሪካው የሚገዙበት መንገድ እየተመቻቸ እንደኾነ ነግረውናል።
የቁጥጥር ሥራውም ቢኾን በሚኒስቴር መ/ቤቱ የተመደቡ አካላት በፋብሪካዎች መኖራቸውን እና አጠቃላይ በተፈለገው መንገድ እያመረቱና እያከፋፈሉ ነው የሚለውን እየተቆጣጠሩ ነው ብለዋል። ከዚያ ባለፈ ፋብሪካዎቹ በቀን በተቀመጠላቸው የምርት ልክ እያመረቱ ነው ወይ የሚለውን ለሚኒስቴሩ እንዲያቀርቡ እንዲያቀርቡ እያደረን ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-10-03
