አጠቃላይ የቤተሰቦን ዕድሜ ደምረት ያውቃሉ? ከወደ ስፔን የ አንድ ቤተሰብ ዕድሜ ተደምሮ 1058 መድረሱን ሰማንና ልናጋራቹ ወደድን ።
ነገሩ እንዲ ነው ። ነዋሪነታቸው በስፔን የሆነ በአጠቃላይ 12 የሚሆኑ ወንድምና እህቶች በአንድ የቤተሰብ ስብስብ ላይ ቁጭ ብለው እየተጫወቱ ከመሀላቸው ያለ አንድ ወንድማቸው በ እጅ ስልኩ አንድ ዜና ይመለከታል ።
ዜናው 12 የሚደረሱ የቤተሰብ አባላት የእያንዳዳቸው እድሜ ተደምሮ አጠቃላይ 921 በመሙላቱ የ አለም ክብረወሰንን ሰበሩ የሚል ነበር ። ታዲያ ይህ ቤተሰብ በዚህ ዜና በመገረም የኛስ ቤተሰብ አጠቃላይ ዕድሜ ስንት ይሆን በማለት ቆጠራ ገቡ ።
በዛ ቤተሰብ ውስጥ የነበረው ትንሹ ዕድሜ 76 ሲሆን ትልቁ ደግሞ 97 ነበር ። በመሀል ያሉትም 80 ዐመታትን በዚች ምድር ያሳለፉ ናቸው ። ቆጠራው ተጠናቀቀ ። የመጣውም ውጤት ሁሉንም አስገረመ ።
የዚህ ቤተሰብ አጠቃላይ እድሜ 1058 ዐመት ሆነ ። 921 በመሆን በአለም ክብረወሰን መዝገብ የተጻፈው የዛ ቤተሰብ ታሪክ በአዲሶቹ የ ዕድሜ ባለጸጎች እንደሚታጠፍ እርግጠኛ ሆኑ ። ጊዜ ሳይፈጁም የቤተሰባቸውን ስም በደማቁ ለማጻፍ ማስረጃቸውን ይዘው ወደሚመለከተው አካል አመሩ ።
የ ዐለም ክብረወሰን መዝጋቢው አካል በመጣለት ማስረጃ በመገረም 921 ትልቁ የዐለማችን ቤተሰብ ዕድሜ ብሎ በመዝገቡ ላይ ያሰፈረውን የ አንድ ወር ቆይታ እንኳን ሳይሞላው ለማንሳት ተገደደ። የ 1058 ዐመት የ ዕድሜ ባለጸጋዎች በቦታው ሰፈሩ ።
በዮሴፍ ከበደ
2022-10-03
