ሀገሬ ቲቪ

በድሬዳዋ ይጀመራል የተባለው ነፃ የንግድ ቀጠና

አምና ብለን በተሻገርነው 2014 ዓ.ም. በወርሃ ነሐሴ በኢትዮጵያ አዲስ ነገር ተዋወቀ። በርግጥ ቀሪው ዓለም ለዚህ አዲስ እንዳልሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ያወሳሉ፤ ነፃ የንግድ ቀጠና (free trade zone)።

ከአዲስ አበባ በ 450ኪሎ ሜትሮች እርቃ የምትገኘው የበርሃዋ ገነት ድሬዳዋ ደግሞ ለዚህ ቀጠና መቀመጫነት የተመረጠች ከተማ ነበረች።

ከጅቡቲ ወደብ በስተደቡብ ምዕራብ 320 ኪሜ ርቀት ላይ የሚገኘው ይህችው የንግድ መናኸሪያ በነሐሴ 8 2014 ዓ.ም. በይፋ ነፃ የንግድ ቀጠና (free trade zone)።

የቦታው ቅርበት ወደቦች፣ የገበያ አቅም፣ ትልቅ የጭነት አቅም እና የመልቲሞዳል ሎጅስቲክስ ስራዎች ተስማሚነት ደግሞ ከተማዋ ለመመረጧ እንደምክንያት ይጠቀሳሉ።

ስለ ነፃ የንግድ ቀጠና ለሎጀስቲክ ዘርፉ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ፍሬት ፎርዋርድስ ኤንድ ሺፒንግ ኤጀንጽ አሶሴሽን እና በትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካን መካከል ተፈርሟል።

ፕሮጀክቱ በዘርፉ ያለውን የሰው ኃይል አቅም እና እውቀት ለማሳደግ ያለመ ስለመሆኑም በስምምነቱ ላይ ተነስቷል።

በስምምነቱ ላይ ያናገርናቸው የኢትዮጵያ ፍሬት ፎርዋርድስ ኤንድ ሺፒንግ ኤጀንጽ አሶሴሽን ፕሬዚዳንት ወ/ ሮ ኤልሳቤጥ ጌታሁን ስለ ነፃ የንግድ ቀጠና ምንነት ይህንን ብለውናል።

ይህ ተቋማት ምርቶቻቸውን እና አገልግሎቶቻቸውን በነፃ የሚገበያዩበት ቀጠና በሀገራችን ላይ መዘጋጀቱ እሴት ለሚጨመርባቸው ቴክኖሎጂዎች በር ከመክፈቱም ባለፈ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን መሳብ እና የከተማ መስፋፋትን ከማምጣቱም ባለፈ እንደ ሀገር ያለውን ፋይዳም እንዲህ አስረድተዋል።

ከተማዋ ለጅቡቲ ወደብ ካላት ቅርበት እና በከተማዋ ያለው ኤርፖርት ዓለም አቀፍ በረራዎችን ማስተናገድ መቻሉ ለቀጠናው የተሻለ እድልን የሚፈጥር ስለመሆኑም ሰምተናል።

የነፃ የንግድ ቅተናን ለማስተናገድ በዘርፉ ያለውን የሰው ኃይል ብቁ ለማድረግም ተቋማቸው ስራዎችን እየሰራ ስለመሆኑ ወ/ ሮ ኤልሳቤጥ ጨምረው ነግረውናል።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-10-04