ሀገሬ ቲቪ

በአዲስ አበባ የተገነባው የሳይንስ ሙዚየም ተመረቀ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አዲስ የተገነባውን የሳይንስ ሙዚየምን በዛሬው ዕለት መርቀው ከፍተዋል።ሙዚየሙ የተገነባው በ6.78 ሄክታር መሬት ሲሆን ሁለት ግዙፍ ህንጻዎችም ያሉት ነው ።

ከተፈጥሮ ስርዓት ጋር ተስማሚ ሆኖ የተገነባው ይህ ሙዚየም ከጸሐይ ብርሀን የኤሌክትሪክ ሀይል እንዲያገኝ ተደርጎ ነው የተገነባው።በሙዚየሙ ለሚቀጥሉት ተከታታይ ሳምንታት የሚቆይ አውደ ርዕይም ተጀምሯል ።

በተያያዘ ዜና በኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የተዘጋጀው የፓን አፍሪካን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተገኝተዋል ።

ኮንፈረንሱ እየተካሄድ የሚገኘው ዛሬ ተመርቆ በተከፈተው የሳይንስ ሙዚየም ውስጥ ነው። ኮንፈረንሱ ለሁለት ቀናት እንድሚቆይም ተገልጿል።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-10-04