የኢትዮጵያ አየር መንገድ በላልይበላ የሀገር ውስጥ በረራውን ዛሬ ይጀምራል ተባለ። የአማራ ክልል ቱሪዝም ቢሮ አየር መንገዱ ከአራት ወራት በላይ አቋርጦት የነበረውን በረራ ዛሬ እንደሚጀምር አስታውቋል። የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ጣሂር ሙሀመድ እንደተናገሩት የሕወሓት ቡድን የላልይበላ ከተማን በወረራ በያዘበት ወቅት የላልይበላ አውሮፕላን ማረፊያን ማውደሙ ይታወቃል። የወደሙ መሠረተ ልማቶችን መልሶ በመገንባት አውሮፕላን ማረፊያው ለገና በዓል አገልግሎት ይሰጥ ዘንድ ዝግጁ ሆኗል። በዚህም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ከሲቪል አቪዬሽን እንዲሁም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው መሰል ተቋማት ጋር በመስራት ወደ ስራ እንዲገባ ተደርጓል።
በሀገሬ ቲቪ
2022-01-03
