ሀገሬ ቲቪ

በአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሃመር ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው

በአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሃመር የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በአፍሪካ ህብረት መሪነት በሚካሄድ የሰላም ድርድር አማካኝነት መቋጪያ እንዲያገኝ ግፊት ለማድረግ ወድ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው።

ልዩ ልዑኩ በጉዳዩ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር እንደሚመክሩ ተገልጿል። ልዩ ልዑኩ ወደ ኢትዮጵያ ሲያመሩ በወር ወስጥ ለሁለትኛ ግዜ ነው።

ማይክ ሃመር በዚሁ ጉዳይ ላይ ለመምከር እና በህብረቱ መሪነት የሚካሄደው ድርድር እንዲሳካ ድጋፍ እንዲያደርጉ ለመጠየቅ አስቀደመው ወደ ደቡብ አፍሪካና ኬንያ እንደሚጓዙ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ቢሮ ያወጣው መግለጫ ያሳያል።

በተያያዘ ዜና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒዮ ብሊንከን የስሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እልባት ማግኘት በሚችለበት ጉዳይ ላይ ከአዲሱ ተመራጭ የኬንያ ፕሬዘዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር በስልክ መውያየታቸው ተዘግቧል።

በብሩክ ያሬድ
2022-10-04