
የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች በመጪው ህዳር በግብጽ በሚካሄደው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ የጋራ አቋም ለመያዝ እየመከሩ ነው።
ከ40 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡት እነዚህ አካላት በኮንጎ ኪሻሳ እያደርጉት ባለው ስብሰባ በአፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ እየደረስ ያለውን ጫና ለመቋቋም እንዲቻል የበለጸጉት ሀገራት ተገቢውን የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ የጋራ አቋም ይይዛሉ ተብሏል።
የዲሞክራቲክ ኮንጎ ጠቅላይ ሚንስትር ጄን ሚቻል ሳማ ጉዳዩ የልጆቻችንና የልጅ ልጆቻችንን ህልውና የሚፈታተን በመሆኑ ከምዕራባውያኑ አፋጣኝ የካሳ ክፍያ እንሻለን ይህም በግብጹ ጉባኤ ተገቢውን ምላሽ ሊያገኝ ይገባል ብለዋል።
በብሩክ ያሬድ
2022-10-04