ሀገሬ ቲቪ

ሰሜን ኮርያ ወደ ጃፓን ሚሳየል አስወነጨፈች

ሰሜን ኮርያ 4500 ኪሎሜትር የሚምዘገዘጉ ሁለት ሚሳዬሎችን በጃፓን ሰማይ ላይ አስወነጨፈች።

ሚሳዬሎቹ ማረፊያቸው የፓስፊክ ውቅያኖስ ቢሆንም በሰሜን ጃፓን ሆካኢዶ ደሴት ፍንዳታውና ንውጽውጽታው እንደተሰማ ተነግሯል።

ጃፓናን አሜሪካ የሰሜን ኮርያን ድርጊት ጸብ ሽጫሪነት ነው ሲሉ ወቅሰዋል። ሰሜን ኮርያ በጃፓን ሰማይ ላይ እንዲህ ያለ የሚሳየል ሙከራ ስታደርግ ከ2017 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል።

ሙከራውን ለማድረግ ያነሳሳት ጃፓን ደቡብ ኮርያና አሜሪካ የጋራ የጦር ልምምድ ማድረገቸው ሳይሆን አይቀርም እየተባለ ነው።

በብሩክ ያሬድ
2022-10-04