የአፍሪካ ህብረት ለፌደራል መንግስት እና ለሕወኃት ኃይሎች የላከውን የሰላም ጥሪ የፌደራል መንግስቱ መቀበሉን አስታወቀ።
ለተላከው የሰላም ጥሪ የሕወኃት ኃይሎችም አወንታዊ ምላሽ ይኖራቸዋል ተብሎም ይጠበቃል።
በደቡብ አፍሪካ ሊካሄድ እንደሚችል የተጠቆመው ድርድሩ በኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ፣ ኡሁሩ ኬንያታ እና የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ፉምዙሌ ምላምቦ ንግኩካን አደራዳሪነት ይካሄዳል።
የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን መንግስት የአፍሪካ ህብረት ግብዣን ስለመቀበሉ ያሳወቁ ሲሆን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ደግሞ ግጭቱን በሰላም ለመፍታት መንግስት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
በአፍሪቃ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ለዚሁ ጉዳይ ወደ ደቡብ አፍሪካ ማምራታቸው ይታወሳል።
በሳምሶን ገድሉ
2022-10-05
