ሀገራችን ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪየሽን ድርጅት ምክር ቤት አባል እንድትሆን በካናዳ ሞንትሪያል እየተካሄደ ባለው 41ኛው የዓለም አቀፉ የሲቪል አቪየሽን ድርጅት ስብሰባ ላይ ተመረጠች።
ምክርቤቱ (ካውንስሉ) ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባኤው ሲሆን በየሶስት ዓመቱ በሚመረጡ በ36 ሀገራት ይዋቀራል።
ሀገራችን የምክር ቤቱ አባል ሆና መመረጧ በዘርፉ ላይ የሚወጡ ዓለም አቀፋዊ ፖሊሲዎችን እና ስትራቴጂዎችን አስቀድሞ በመገንዘብ ወደ ትግበራ እንድትገባ ብሎም ለታዳጊ፣ ወደብ አልባ እና ትናንሽ የደሴት ሀገሮች ድምጽ እንድትሆን ያስችላታል ሲል መረጃውን ያደረሰው የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ነው።
በሳምሶን ገድሉ
2022-10-05
