ሀገሬ ቲቪ

የደራው የጨርቃጨርቅ ወጪ ንግድ

ከጨርቃ ጨርቅ ገበያ 78.5 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ፡፡ የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በአምስት ወራት ውስጥ ነው የተለያዩ የጨርቃጨርቅ ምርቶችን ወደ ውጭ ገበያ በመላክ ገቢውን ያገኘው፡፡ ይህም በባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው 65.7 ሚሊዮን ዶላር ጋር ሲነጻጸር የ 12.8ሚሊዮን ዶላር ብልጫ አለው፡ በዚህም በአምስት ወራት 79.5 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ዕቅድ ተይዞ፣ የዕቅዱን 98 በመቶ ማሳካት ተችሏል፡፡ ገቢው የተገኘው ድርና ማግ፣ጨርቃጨርቅ፣አልባሳትና ባህላዊ አልባሳትን ወደ ጀርመን፣ጣሊያን ፣አሜሪካና ሌሎች የእሲያ እና የአፍሪካ ሀገራት በመላክ ነው፡፡ በጦርንቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው እንደ ኮምቦልቻ ያሉኢንደስትሪዎች ግን ገቢ መሸብሸብ እንዳልተቻለ ተሰምቷል፡፡ በተመሳሳይ ለዘርፉ ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኙት በመቀሌ የሚገኙ 6 ትላልቅ ኢንደስትሪዎችም ገቢ አለመሰብሰቡ ተገልጿል፡፡ በ2014 ምርት ዘመን ከጨርቃጨርቅ ኢንደስትሪው 223 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዷል፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2022-01-04