መንገድ ያደርሳል፤ መንገድ ይመልሳል። የተሽከርካሪ መንገዶች ደግሞ ብዙዎችን በዓለም ዙሪያ ያገናኛሉ። በእነዚህ የተሽከርካሪ መንገዶች ላይ በምሽት ማሽከርከር በአንዳንዶቹ አስደሳች በሌለኞቹ መንገዶች ደግሞ አስፈሪም ይሆናል።
ታርማክ ላይን ማርኪንግ የተሰኘ የአውስትራሊያ ተቋም ግን ምን በወጣዎ ነው የምሽት ጉዞዎ አስፈሪም አሰልችም የሚሆንብዎ ይልቁንስ የመዝናኛ አማራጭ ይሆንወታል እያለ ነው።
ተቋሙ የምሽት ጉዞን በሳይንስ ፊክሽን ፊልሞች እንደሚያዩት እንደመጓዝ እንዲሰማዎ የሚያደርግ ፈጠራን ለማምጣት እየሰራሁ ነው ባይ ነው።
በቅርቡ በሀገረ አውስትራሊያ ይሄንንው ለፈጠራዊ መዝናኛነት የማዋል ስራውን የመጨረሻ ሙከራውን በአንድ ኪሎ ሜትሮች ርቀት በተዘረጉ የፎቶሉምኒሰንት ቅቦች በገጠራማ መንገዶች ላይ አድርጓል።
የፎቶሉምኒሰንት ቅቦቹ በቀን ብርሃንን በመሰብሰብ ነው በምሽት የመንገዱን ዕይታ ወደ ማራኪነት የሚቀይሩት። በዚህም ሳይንሳዊ ስራ አያይ በምሽት መጓዝ ማለትዎን ትተው ደጋግሜ በተጓዝኩ የሚያሰኝ ስሜት በአሽከርካሪዎች ላይ ይፈጥራል ተብሎለታልም።
የምሽት አሽከርካሪዎችን የመስልቸት ስሜትንም መንገዶቹ ላይ የሚፈጠረው ማራኪ የምሽት ዕይታ መቀነስ ይችላል እየተባለለትም ነው።
ይሄንን በአይነቱ አዲስ የሆነውን ስራውን ታርማክ ኦምኒግሪፕ እና ቫይክ ሮድስ ከተሰኙ ተቋማት ጋር እየሰራ ስለመሆኑም ተነግሯል።
በአውስትራሊያ ዋና ከተማ ቪክቶሪያ ደቡብ ምስራቅ የገጠር መንገዶች ላይ የተሞከረው የመንገድ ቅብ በምሽት የሚፈጥረው ዕይታ በማህበራዊ መገናኛዎች ላይ ከተጋራ በኋላ የብዙዎችን ቀልብ መሳብ ችሏል።
ይሄንንው ስራ ሀገራት እና ትልልቅ የቢዝነስ ተቋማት ለመግዛት ሊሯሯጡ እንደሚችልም ገና በሙከራ ጊዜው ማራኪነቱ ትልቅ ጥቆማን ሰጥቷል።
ይሄንንው ፈጠራውን እያመረተ ያለው ታንማርክ አሽከርካሪዎች የመንገድ ምልክቶችን በቀላሉ እንዲመለከቱ ከማስቻሉም በላይ ወደ መስቀለኛ መንገዶች እና እጥፋቶች ሲደርሱ ለሚጓዙበት መንገድ አዲስ የሆኑ አሽከርካሪዎች ፈጣን ምላሽ መስጠት እንዲችሉ ያስችላቸውል ተብሏል።
በአብርሃም በለጠ
2022-10-06
