391 የሚደርሱ ሕገወጥ የሐዋላ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ ።ብሔራዊ ባንክ 391 የሚደርሱ ሕገወጥ የሐዋላ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች የባንክ ሂሳባቸው ተዘግቶ ክስ የመመስረት ሂደት እንደተጀመረ አስታወቀ።
ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ ጉዳዩን አስመልክተው በሂልተን ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው በዚህ ህገወጥ ተግባር ተሳታፊ የሆኑ የባንክ ኃላፊዎችና ሠራተኞችም እንዳሉ ጠቅሰው በነዚህ አካላት ላይ አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ጠቁመዋል።
ይሕን ሕገወጥ ድርጊት ለሚጠቁሙ ዜጎች ደህንነታቸውን በጠበቀ መልኩ የወሮታ አከፋፈል ስርዓት የተዘጋጀ መሆኑንም ገልጸዋል።
በዮሴፍ ከበደ
2022-10-07
