ሀገሬ ቲቪ

16 ትምህርት ቤቶች ሊገነቡ ነው

ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ከትምህርት ሚኒሰቴር ጋር በመተባበር በአራት ክልሎች 16 ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ሥምምነት አድርገዋል። እነዚህ ት/ቤቶች ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ይገነባሉ ተብሏል።

ትምሕርት ቤቶቹ በአፋር፣ ሶማሌ፣ አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ይገነባሉ። በዓመት በአማካይ ስምንት ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ ተብሏል፡፡

የግንባታ ስራው በኦሮሚያ እና ሱማሌ ክልሎች የአዳዲስ ት/ቤቶች መገንባትን ያካተተ ሲሆን በአፋር እና አማራ ክልሎች ደግሞ ኣዳዲሰ ከሚሰሩ ት/ቤቶች በተጨማሪ በጦርነት የተጎዱ የት/ቤት ህንፃዎችን በአዲስ የመተካት ስራንምያካትታልባለፉት ሁለት አመታት በጦርነት እና ግጭት ምክንያቶች በአፋር፣ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ኦሮሚያ እና ደቡብ ክልሎች ከ1,336 በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መዉደማቸዉ ይታወቃል፡፡

በሙሉጌታ በላይ
2022-10-07