ሀገሬ ቲቪ

ከዓለም አቀፉ ምጣኔ ሀብት የተጋረጠበት አደጋ

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ ዓለም አቀፍ ምጣኔ ሀብት 4 ትሪሊየን ዶላር ጉድለት ሊያመጣ ይችላል አለ። የዓለም ምጣኔ ሀብት ከፍተኛ አደጋ የተጋረጠበት በመኾኑ ነው ይህ ጉድለት ሊከሰት ይችላል የሚል ትንበያውን ያስታወቀው።

ሁኔታው “ከመሻሻል ይልቅ የመባባስ ዕድሉ ሰፊ ነው” ሲሉ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂዬቫ መናገራቸውን የቻይናው የዜን ምንጭ ሽንዋ ዘግቧል። ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተጽዕኖ የሩሲያና ዩሬን ጦርነት ተጨምሮ ነገሩን ይብስ አክብዶታል ተብሏል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-10-07